የ2019 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ
ባህር ዳር | ህዳር 03/2019 ዓ.ም
የጢስ እሳት ውሀ ስራዎች የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የካምፓኒው የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በዛሬው እለት ተግምግሟ፡፡
ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት በቁልፍ አፈፃፀም አመላካች ያቀዳቸውን የፋይናንስ፣ የገቢ ማስገኛ ተግባራት፤ የአስተዳደራዊ ጉዳዮች እና የገበያ ልማት ተግባራት አፈፃፀም ላይ ትኩረት በማድረግ የገመገመ ሲሆን ከዚህ የአፈፃፀም ሪፖርት ትምህርት በመውስድ በዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታቀደውን ውጤት ለማምጣት ከአሁኑ በትጋት መስራት እንደሚገባ የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ ጫኔ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኩባንያው ሰራተኞች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
