የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምስጉን ግብር ከፋዮች ሃገር አቀፍ እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ ኩባንያችን እውቅና ተሰጠው።

ኩባንያው በተሰማራባቸው የውኃ ዘርፍ  ተግባራት የህብረተሰቡን የመጠጥ ውኃ አቅርት ችግሮች ከመፍታት በተጨማሪ አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ አውታር ዝርጋታ ፕሮጀክቶችን በጥራት በማከናወን የክልሉን ልማት በማፋጠን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡  ከዚህ በተጨማሪ በየዓመቱ ያስገመዘበውን ትርፍ በታማኝነት ለሚመለከተው ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት በማሳወቅና በወቅቱም በመክፈል እንደተቋም ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ይህንን መነሻ በማድረግ ሃምሌ 15/2011 ዓ.ም የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምስጉን ግብር ከፋዮች ሃገር አቀፍ እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ ኩባንያችን በሲሊቨር ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን የምስጉን ግብር ከፋይ እውቅና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ የተቀበልን ሲሆን መላው የኩባንያው ሰራተኞችና አመራሮችና ላረጋችሁት ጥረት ኩባንያው ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡

Hits: 2076

Who's online

We have 86 guests and no members online

Similar Items