ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች እ.አ.አ. በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞቹን እውቅና ሰጥቷል

ኩባንያው በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው ከፍተኛ አፈጻጸምና የ2019 እቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ደሴት ሎጅ ከሰራተኞቹ ጋር ባዘጋጀው የግብዣ ፕሮግራም ላይ የጋፋት ኢንዶውመንት አመራሮች፤ የኩባንያው የቦርድ አባላት፤ የአጋር ድርጅቶች አመራሮችና የእህት ኩባንያዎች አመራሮች በተገኙበት በበጀት ዓመቱ ለነበረው ከፍተኛ አፈጻጸም የተሻለ አፈጻጸም በቡድንም በግልም ለነበራቸው ለ22 ሰራተኞቹ የእውቅናና ማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 4ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ለእያንዳንዳቸውም ብር 5000.00 ማበረታቻ እንዲሆን ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

Tisisat Information Management System (TIMS) 

 ኩባንያችን ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች ራሱን ከቴክኖሎጅ እድገት ጋር ለማላመድ የቢሮ ስራዎችንና የመረጃ ልውውጥ ተግባራትን በአንድ በማቀናጀት ወጥነት ያለው የመረጃ ስርዓትና የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ሶፍትዌር ማለትም በኩባንያው አጠራር ’’Tisisat Information Management System (TIMS) በሚል በመሰየም የሙከራ ስራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት ጀምሯል፡፡

በቀጣይም ሶፍተዌሩን እስከ ፕሮጀክት ድረስ ለማውረድና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል አቅም በመግባት አጠቃላይ ስራዎችን በሲስተም የታገዘ ለማድረግ ኩባንያው ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ በመሆኑም መላው የኩባንያው አመራሮችና ባለሙያዎች ለትግበራው ውጤታማነት የሚጠበቅባቸሁ አስተዋጽኦ ወሳኝ ሚና ስለሚኖረው ኩባንያው ስራችን በዚሁ ሲስተም መሰረት እንዲከናወኑ ከሚያሳውቅበት ቀን ጀምሮ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ቴክኖሎጅውን እውን በማድረግና በውጤቱም ስራችንን የተቀናጀና የተቀላጠፈ ማድረግ አርአያ መሆን ይጠበቅብናል፡፡

 

Hits: 74700

Who's online

We have 144 guests and no members online

Similar Items